ከዑመር ቢን ኸጧብ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: ነቢዩ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- እንዲህ ብለዋል: "በአላህ ላይ ትክክለኛውን መመካት ብትመኩ ኖሮ ወፍን እንደሚለግሰው ለናንተም ሲሳይን ይለግሳቹህ ነበር። (ወፍ) ተርባ ማልዳ ትወጣለች። ሆዷ (በጥጋብ) ሞልቶ ትመለሳለች።" ሶሒሕ ነው። - رواه الإمام أحمد والترمذي والنسائي وابن ماجه وابن حبان في صحيحه والحاكم
explain-icon

ትንታኔ

ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም በዱንያዊም በዲናዊም ጉዳይ ጥቅምን በማምጣትና ጉዳትን በመከላከል ረገድ በአላህ ላይ እንድንደገፍ እያነሳሱን ነው። ምክንያቱም ከአላህ በስተቀር የሚሰጥም፣ የሚከለክልም ፣ የሚጎዳም፣ የሚጠቅምም የለምና ነው። ጥቅሞችን የሚያመጡና ጉዳቶችን የሚከላከሉ ሰበቦችን በአላህ ላይ ከእውነተኛ መመካት ጋር እንድንፈፅምም አነሳሱ። ይህንን በማንኛውም ወቅት ከፈፀምን አላህ ወፍን በንጋት የተራበች ሆና ወጥታ ከዚያም በምሽት ሆዷ ሞልቶ በመመለስ እንደሚቀልባት እኛንም ይቀልበን ነበር። ይህም የወፏ ድርጊት ያለመሳነፍና መዳከም ሲሳይን ለመፈለግ የሰራችው የሰበብ አይነት ነው።

explain-icon

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  • የመመካት ትሩፋትንና መመካት ሲሳይን ከሚያመጡ መንስኤዎች መካከል ትልቁ እንደሆነ እንረዳለን።
  • መመካት ሰበቦችን ከመፈፀም ጋር አይጋጭም። ምክንያቱም እሳቸው ሲሳይ ለመፈለግ ማልዶ መውጣትና አምሽቶ መመለስ ትክክለኛውን መመካት እንደማይጣረሰው ተናግረዋልና።
  • መመካት የቀልብ ተግባር ነውና ሸሪዐ ለቀልብ ተግባራት ትኩረት መስጠቱን እንረዳለን።
  • በሰበብ ላይ ብቻ መንጠልጠል የዲን ጉድለት ሲሆን ሰበቦችን መተው ደግሞ የአይምሮ ጉድለት ነው።