የተከበረው ቁርኣን ምዕራፎች በነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን ላይ ሲወርዱ የሚጠናቀቁበትና ከሌላው ምእራፍ የሚለዩበትን መንገድ ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን አያውቁም ነበር። ይህ ግን {ቢስሚላሂ አር-ረሕማኒ አር-ረሒም} እስክትወርድ ድረስ ነበር። እሷ ከወረደች በኋላ ያለፈው ምእራፍ እንደተጠናቀቀችና {ቢስሚላሂ አር-ረሕማኒ አር-ረሒም} ለአዲስ ምዕራፍ መክፈቻ እንደሆነች አወቁ በማለት ኢብኑ ዐባስ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- ገለፁ።