የአማኞች መሪ ዑሥማን ቢን ዓፋን (ረዺየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - ቀብር ላይ የቆሙ ጊዜ በእንባቸው ፂማቸው እስኪረጥብ ድረስ ያለቅሱ ነበርና እንዲህ ተባሉ: ጀነትና እሳት ሲወሱ ጀነትን ከመናፈቅ ወይም እሳትን በመፍራት ምክንያት ሳታለቅስ ቀብር ላይ ሲሆን ታለቅሳለህ? እርሳቸውም "ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ቀብር ከመጪው አለም ማረፊያዎች መካከል የመጀመሪያው ማረፊያ እንደሆነ ተናግረዋል። ከቀብር ቅጣት ከዳነና ከተገላገለ ከርሱ በኋላ ያለው ማረፊያ ቀላል ነው። ከቀብር ቅጣት ካልዳነ ደግሞ ከርሱ በኋላ ያለው ቅጣት ከርሱ የበረታ ነው።" ብለዋል አለ።