ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: "ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል: ‹ባሏ ለሞተባትና ለሚስኪን የሚለፋ ሰው ልክ በአላህ መንገድ እንደሚታገል ሰው አምሳያ ወይም ልክ ሌሊት እየሰገደ ቀኑን እንደሚፆም አምሳያ ነው›" ሶሒሕ ነው። - ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
explain-icon

ትንታኔ

ባሏ ለሞተባትና የሚያስፈልጋትን ጉዳይ የሚያሟላላት አንድም ሰው ለሌላት ሴት እና ተረጂ ለሆነ ሚስኪን ጥቅማቸውን በሟሟላት የቆመ እንዲሁም አላህ ዘንድ ምንዳን በማሰብ ለነርሱ ወጪ የሚያደርግ ሰው በምንዳ ደረጃ ልክ በአላህ መንገድ እንደሚታገል ወይም ለተሀጁድ ሶላት ሳይደክም እየቆመ ምንም ቀን ሳያፈጥር እንደሚፆም ሰው አምሳያ መሆኑን ነቢዩ (የአሏህ ሶለዋትና ሰላም በሳቸው ላይ ይስፈንና) ተናገሩ።

explain-icon

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  • በመተጋገዝ፣ ሀላፊነትን በመወጣትና የደካሞችን አስፈላጊ ጉዳዮች በማሟላት ላይ መነሳሳቱን እንረዳለን።
  • አምልኮ ሲባል ሁሉንም መልካም ስራ ይሰበስባል። ከአምልኮዎች መካከልም ባሏ ለሞተባት ሴትና ለሚስኪን ጥቅም መልፋት አንዱ ነው።
  • ኢብኑ ሁበይራ እንዲህ ብለዋል: "ከዚህ ሐዲሥ የተፈለገው ከፍ ያለው አላህ የታጋይ (የሙጃሂድ)ና እየፆመ ሌሊት የሚቆምን ሰው ምንዳ በአንድ ጊዜ ይሰበስብለታል ማለት ነው። ይህም ባሏ ለሞተባት ሴት የባሏን ቦታ ተክቶ ስለተወጣ … ራሱን ችሎ መቆም ለተሳነው ሚስኪንም የተረፈውን ቀለብ ወጪ አድርጎ በአቅሙ ስለመፀወተ የሰጠው ጥቅም ፆም፣ የሌሊት ሶላትና ጂሀድን የሚመጥን ሆነ።"