ከዐምር ቢን ሱለይም አልአንሷሪይ እንደተላለፈው እንዲህ አለ: "አቡ ሰዒድ እንዲህ እንዳለ እመሰክራለሁ: 'የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ እንዳሉ እመሰክራለሁ: "ለአቅመ አዳም በደረሰ ሰው ላይ ሁሉ የጁሙዓ ቀን መታጠብ፣ ጥርሱን ሊፍቅና ካገኘም ሽቶ መቀባቱ ግዴታ ነው።" ሶሒሕ ነው። - ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።