ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እየነገሩን ያሉት: ዉዱእን ማዕዘናቶቹን አሟልቶ፣ ሱናዎቹንና ስነስርአቶቹንም በመፈፀም አሳምሮ ካደረገ በኃላ ወደ ጁሙዓ ሶላት በመምጣት ዝም ብሎ ኹጥባውን ያዳመጠና ከዛዛታ ነገር ዝም ያለ ሰው አላህ ለርሱ የአስር ቀን ትናንሽ ወንጀሎቹን ይምረዋል። እነሱም ከሰገደው ጁሙዓ ቀን እስከሚቀጥለው ጁሙዓ ድረስና የተጨማሪ ሶስት ቀን ወንጀል ነው። ምክንያቱም መልካም ስራ አስር አምሳያውን ያስመነዳልና። ቀጥለውም ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ኹጥባ ላይ ለሚነገረው ተግሳፅ የልብን ትኩረት ከመንፈግ፣ በሰውነት ከመጫወት፣ ጠጠርን በመነካካትና በሌሎችም በሚጠምዱ የጨዋታ አይነቶች ከመዘናጋት አስጠነቀቁ። ይህንን የፈፀመ በርግጥም የጁሙዓውን የተሟላ ስራ ውድቅ አድርጎታል። ውድቅ ስራ የሰራ ሰውም ከተሟላ የጁሙዓ ምንዳ ለርሱ ድርሻ የለውም።