ከዑባዳህ ቢን ሷሚት (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል: "የመጽሐፉን መክፈቻ (ፋቲሓን) ያላነበበ ሰው ሶላት የለውም።" ሶሒሕ ነው። - ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
explain-icon

ትንታኔ

ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) የፋቲሓን ምዕራፍ በመቅራት ካልሆነ በቀር ሶላት ትክክለኛ እንደማትሆን ገለፁ። ፋቲሓ በሁሉም ረከዓዎች ከሚደረጉ የሶላት ማእዘናት መካከል አንዷ ናት።

explain-icon

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  • ፋቲሓን መቅራት እየቻለ ፋቲሓን ከመቅራት ፋንታ ሌላ ምእራፍ መቅራት አያብቃቃም።
  • አውቆም ሆነ ሳያውቅ ወይም ረስቶ ፋቲሓ ያልተቀራበት ረከዓ የተበላሸ መሆኑን እንረዳለን። ምክንያቱም ፋቲሓ የሶላት ማእዘን ናት። ማእዘን ደግሞ በማንኛውም ሁኔታ ላይ ቢሆን አይወድቅም።
  • ተከታይ የሆነ ሰው ኢማሙን ሩኩዕ ላይ ቢደርስበት ፋቲሓን የመቅራት ግዴታው ይነሳለታል።