ከዐብደሏህ ቢን ዓምር (ረዲየሏሁ ዓንሁማ) አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል፡ "በቃል ኪዳን ስር ያለን (ሙዓሀድን) የገደለ ሰው የጀነትን ሽታ አያሸትም። የጀነት ሽታዋ የሚገኘው አርባ አመት ከሚያስኬድ ርቀት በኋላ ነው።" ሶሒሕ ነው። - ቡኻሪ ዘግበውታል።