ከአቡ ሰዒድ አልኹድሪይ (ረዲየላሁ ዐንሁ) -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንዲህ አሉ፦ «የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል፦ "ከናንተ በፊት የነበሩትን (ሕዝቦች) ጎዳና ስንዝር በስንዝር፣ ክንድ በክንድ ትከተላላችሁ። የወከሎ ቤት (ጉድጓድ) ቢገቡ እንኳ ትከተሏችኋላችሁ።" እኛም "የአላህ መልክተኛ ሆይ! ክርስቲያኖችንና አይሁዶችን ነውን?" አልናቸው። እርሳቸውም "ታዲያ ሌላ ማን ነው?" አሉን።» ሶሒሕ ነው። - ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።