የአማኞች እናት ዓኢሻ - አላህ መልካም ሥራዋን ይውደድላትና - ስለአንዳንድ የነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ስነምግባር ተናገረች። ከጠቀሰቻቸውም መካከል: እርሳቸው በሁለት ነገሮች መካከል ምርጫ ሲሰጣቸው የሚመርጡት ገሩን ነው። ግን ያ ገር ነገር ወንጀል እስካልሆነ ድረስ ነው። ገር ነገሩ ወንጀል ከሆነ ግን ከሰዎች ሁሉ እጅግ የሚርቁት እርሳቸው ናቸው። ጠንከር ያለውንም ይመርጣሉ። ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ለነፍሳቸው ብቻ ብለው አልተበቀሉም። ይልቁንም የአላህ ክልከላ እስካልተደፈረ ድረስ ስለነፍሳቸው ሐቅ ይቅር የሚሉና የሚያልፉ ነበሩ። ለአላህ ብለው ግን ይበቀሉ ነበር። እጅግ በጣም ለአላህ ብለው የሚቆጡ ነበሩ።