ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) አላህ በሰዎች ላይ ከዋላቸው ፀጋዎች መካከል አብዛኛው ሰው ያለ አግባብ በመጠቀም ስለሚከስርባቸው ሁለት ትላልቅ ፀጋዎች ተናገሩ። የሰው ልጅ የጤንነት ፀጋ ነፃ (ከትርፍ) ጊዜ ጋር አብሮ ሲሰበሰቡለት አብዛኛውን ጊዜ ከአምልኮ ሲሳነፍ ነው የሚገኘው። ይህ ክስረት ነው። የአብዛኛው ሰው ሁኔታም እንዲሁ ነው። ትርፍ ወቅቱንና ጤንነቱን አላህን በማምለክ ከተጠቀመበት ግን ዱንያ የመጪው አለም መዝሪያ ናትና ትርፋማ ይሆናል። ዱንያ ውስጥ ትርፉ በመጪው አለም የሚገኝበት ንግድ አለ። ትርፍ ወቅት ከጊዜ በኋላ መጠመድ ይከተለዋል። ጤንነትም በሽታ ይከተለዋል። ሌላው ቀርቶ እርጅና ብቻ እንኳ መምጣቱ በቂ ነው።