ከአነስ ቢን ማሊክ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: ነቢዩ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- እንዲህ ብለዋል፦ "አላህ ሆይ! ከመጪው አለም ኑሮ ውጪ ኑሮ የለም። ለአንሷሮችና ሙሃጂሮች ማራቸው።" ሶሒሕ ነው። - ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
explain-icon

ትንታኔ

ነቢዩ - የአላህ ሶላትና ሰላም በርሳቸው ላይ ይስፈንና - እውነተኛ ኑሮ በመጪው አለም በአላህ ውዴታ፣ እዝነትና ጀነት ውስጥ ያለው ነው እንጂ ሌላ ትክክለኛ ኑሮ እንደሌለ ተናገሩ። የዱንያ ኑሮ ተወጋጅ ነው። የመጪው አለም ኑሮ ዘውታሪና ቀሪ ነው። ቀጥለውም ነቢዩ - የአላህ ሶላትና ሰላም በርሳቸው ላይ ይስፈንና - ምህረትን፣ መከበርንና መልካምነትን ለእነዚያ ነቢዩን - የአላህ ሶላትና ሰላም በርሳቸው ላይ ይስፈንና - እና ሙሃጂሮችን ላስጠጉትና ገንዘባቸውን ላካፈሉት አንሷሮች በተጨማሪ የአላህን ውዴታና ችሮታ ፈልገው ሃገራቸውንና ገንዘባቸውን ትተው ለተሰደዱት ዱዓ አደረጉላቸው።

explain-icon

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  • ነቢዩ - የአላህ ሶላትና ሰላም በርሳቸው ላይ ይስፈንና - ለዱንያ የነበራቸው ቸልተኝነትንና ሙሉ ለሙሉ ወደ መጪው አለም ራሳቸውን ያዞሩ መሆኑን እንረዳለን።
  • ነቢዩ - የአላህ ሶላትና ሰላም በርሳቸው ላይ ይስፈንና - ጠፊ ከሆነው የዱንያ ጥቅም ኡመታቸው ችላ እንዲል መጣራቸውን እንረዳለን።
  • ሙሃጂሮችና አንሷሮች ምህረት እንዲያገኙ በነቢዩ - የአላህ ሶላትና ሰላም በርሳቸው ላይ ይስፈንና - ዱዓ የተደረገላቸው በመሆናቸው የነርሱ ማዕረግ ከፍታ ተገልፆ እንመለከታለን።
  • አንድ ሰው በሚያገኘው የዱንያ መጣቀሚያ መደሰት የለበትም። ዱንያ ውስጧ ካሉት መከራዎችም ጋር ለመጥፋት ቅርብ ናትና። የመርጋትና የመዘውተርያ አገር የመጪው አለም አገር ነው።