ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና በእንቅልፍ የሚያስደስት መልካም ህልም መመልከት ከአላህ እንደሆነና የሚጠላውንና የሚያሳዝነውን ቅብዥር መመልከት ደግሞ ከሸይጧን እንደሆነ ተናገሩ። የሚጠላውን ህልም የተመለከተ ሰው ወደ ግራው አቅጣጫ ይትፋ፤ ከህልሙ ክፋትም በአላህ ይጠበቅ። ቅብዥሩን ተከትሎ ከሚመጡ ጎጂዎች ሰላም ለመሆን የተጠቀሰውን ማድረግ አላህ ሰበብ ስላደረገው እርሷ አትጎዳውም።