ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ሰዎች በአዛንና በመጀመሪያ ሰልፍ የሚገኘውን ደረጃ፣ መልካምና በረከት ቢያውቁ ኖሮና ከዚያም ለመቀደምና ቅድሚያ ለማግኘት ማነው የሚገባው ለሚለው እጣ መጣጣል ቢጠበቅባቸው ኖሮ እጣ ይጣጣሉ ነበር። ወደ ሶላት በመጀመሪያ ወቅት ቀድሞ የመሄድንም ምንዳ ቢያውቁ ኖሮ ይሽቀዳደሙ ነበር። ወደ ዒሻ ሶላትና ወደ ፈጅር ሶላት መስጂድ የመምጣት ምንዳ መጠኑን ቢያውቁ ኖሮና ወደ መስጂድ መምጣት ቀላል ባይሆንላቸው ኖሮ ህፃን ልጅ እየዳኸ እንደሚመጣው በጉልበታቸው እየዳኹም ይመጡ ነበር አሉ።