ከቡስር ቢን ሰዒድ እንደተላለፈው: ዘይድ ቢን ኻሊድ አልጁሃኒይ -አላህ መልካም ስራውን ይውደድለትና- ቡስር ቢን ሰዒድን ወደ አቡ ጁሃይም -አላህ መልካም ስራውን ይውደድለትና- በሰጋጅ ፊት ስለማለፍ ከአላህ መልክተኛ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - ምን እንደሰማ ሊጠይቀው ላከው። አቡ ጁሃይምም እንዲህ አሉ: «የአላህ መልክተኛ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - እንዲህ ብለዋል: "በሰጋጅ ፊት የሚያልፍ ሰው በርሱ ላይ ያለበትን ወንጀል ቢያውቅ ኖሮ በሰጋጅ ፊት ከማለፍ ይልቅ አርባ መቆም ለርሱ መልካም ይሆንለት ነበር።" አቡ ነድር እንዲህ ብሏል" አርባ ሲል አርባ ቀን ወይም ወር ወይም ዓመት እንደሆነ አላውቅም።" ሶሒሕ ነው። - ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።