የአማኞች እናት ዓኢሻ -አላህ መልካም ስራዋን ይውደድላትና - ነቢዩ -የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- ቤታቸው ውስጥ ስለነበራቸው ሁኔታ ተጠየቁ። ጊዜያቸውን እንዴት ነበር ያሳልፉ ይሰሩ የነበሩት? እርሷም: እንደማንኛውም ሰው እርሳቸውም ሰው ነበሩ። ወንዶች ቤት ውስጥ ይሰሩ የነበሩትን ይሰሩ ነበር። ራሳቸውንና ቤተሰባቸውን ያገለግሉ ነበር። ፍየላቸውን ያልባሉ፣ ልብሳቸውን ይሰፋሉ፣ ጫማቸውን ይጠግናሉ፣ የተቀደደ ባልዲያቸውን ይለጥፋሉ። ሶላት ኢቃም የሚልበት ወቅት ላይ ሲደርሱ ምንም ሳያዘገዩ ወደርሷ ይወጣሉ በማለት መለሰች።