ኡመይማህ ቢንት ሩቀይቃህ ረdiየሏሁ ዐንሃ - አላህ መልካም ሥራዋን ይውደድላትና - እንደተናገረችው እርሷ ነቢዩ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- ዘንድ ከተወሰኑ የአንሷር ሴቶች ጋር ሆና በአላህ ላይ አንዳችንም ላያጋሩ፤ ላይሰርቁ፤ ዝሙት ላይሰሩ፤ በእጆችና በእግሮች መሃል የሚቀጥፉትን ላይፈፅሙ፤ በመልካም ነገር ላይ እርሳቸውን ላያምፁ ከርሳቸው ጋር ቃል ልትጋባ መጣች። ነቢዩም ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- እንዲህ አሉ: "በቻላችሁትና አቅማችሁ በሚፈቅዱ ጉዳዮች ላይ ቃል ተጋባኋቹህ።" እኛም: "አላህና መልክተኛው ለኛ የበለጠ አዛኝ ናቸው። የአላህ መልክተኛ ሆይ! ከወንዶች ጋር ቃል ሲጋቡ እንደሚፈፅሙት ኑ እጅዎን ይዘርጉና በመጨባበጥ ቃል እንጋባዎ።" አልን። እርሳቸውም እንዲህ አሉ: "እኔ ሴቶችን አልጨብጥም። ለመቶ ሴቶች የምናገረውና ቃል የምጋባው ለአንድ ሴት እንደምጋባው ነው።"