ከዐሊይ ቢን አቢጧሊብ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ ብለዋል: «የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ሐር በግራ እጃቸው ወርቅ በቀኝ እጃቸው በመያዝ ከዚያም እነሱን በእጃቸው ከፍ አደረጉና እንዲህ አሉ: "እነዚህ ሁለቱ ከኡመቴ በወንዶቹ ላይ ክልክል ናቸው። ለሴቶቹ ግን የተፈቀደ ነው።"» ሶሒሕ ነው። - رواه أبو داود والنسائي وابن ماجه
explain-icon

ትንታኔ

ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) የሐር ልብስ ወይም ቁራጩን በግራ እጃቸው ይዘው የወርቅ ጌጥ ወይም መሰል ነገር ደሞ በቀኝ እጃቸው ያዙና እንዲህ አሉ: ለወንዶች ሐርና ወርቅ መልበሳቸው ክልክል ነው። ለሴቶች ግን የተፈቀደ ነው።

explain-icon

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  • ሲንዲይ እንዲህ ብለዋል: «(ክልክል) ያሉት በመልበስ መጠቀሙን ነው። ያለበለዚያማ በመመንዘር፣ በመመፅወት፣ በንግድ መጠቀሙ ለሁሉም ፆታ የተፈቀደ ነው። ወርቅን በእቃ መልክ ማድረግና በእቃ መልክ አድርጎ መጠቀሙ ደግሞ ለሁሉም ፆታ ክልክል ነው።»
  • የእስልምና ሸሪዓ ሴቶች ማጌጥና የመሳሰሉትን ከመፈለጋቸው አንፃር ህጉን ለነሱ ሰፋ እንዳደረገላቸው እንረዳለን።