ነቢዩ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- አራት አካላቶች ላይ እርግማንንና ከአላህ እዝነት መራቅን ዱዓ አደረጉባቸው። የመጀመሪያው: የራሷን ወይም የሌላን ሰው ፀጉር በሌላ ፀጉር የምትቀጥል ናት። ሁለተኛው: ሌላ ሰው ፀጉሯን በሌላ ፀጉር እንዲቀጥልላት የምትጠይቅና የምታስቀጥል ናት። ሶስተኛው: ማማርና ውበትን በመፈለግ ፊትን ወይም እጅን ወይም ደረትን የመሰሉ የሰውነት አካላቶችን በመርፌ በመጠቅጠቅ ምልክቱ ሰማያዊ ወይም አረንጓዴ እስኪሆን ድረስ ኩልን ወይም የመሳሰሉትን ቦታው ላይ እየቀባች የምትነቅስ ናት። አራተኛ: ንቅሳት እንዲፈፀምባት የምትፈልግ ናት። እነዚህ ተግባራት ከትላልቅ ወንጀሎች መካከል የሚመደቡ ናቸው።