ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና አላህ ወንጀልነቱን ስላነሳና ይቅር ስላለ አንድ ሙስሊም በውስጡ አስቦ ለተወው መጥፎ ነገር እስካልሰራበት ወይም እስካልተናገረው ድረስ እንደማይያዝበት ተናገሩ። የነቢዩ ሙሐመድ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ኡመት በአይምሯቸው በሚገኝ፣ ልባቸው ላይ ሳይረጋጋና ሳይፀናበት ውስጣቸው ላይ በመጣ መጥፎ ነገር አይያዙም። እንደኩራት፣ መንጠባረርና ንፍቅና ቀልቡ ላይ ከፀናበት፣ በአካሉ ከተገበረ ወይም በምላሱ ከተናገረ ግን ይያዝበታል።