አንድ ሰውዬ ነቢዩን (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ በማለት ጠየቀ "እኛ ለማደን ወይም ለንግድና ለመሳሰሉት በባህር ላይ ጀልባዎችን እንሳፈራለን። ለመጠጥ የሚሆን ትንሽ ውሃንም ከኛ ጋር እንጭናለን። የመጠጡን ውሃ ለዉዱእና ለገላ ትጥበት ከተገለገልን ያልቅብንና የምንጠጣውን አናገኝም። ታዲያ በባህር ውሃ ዉዱእ ማድረግ ለኛ ይፈቀድልናል እንዴ?" ነቢዩም (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ስለባህሩ ውሃ እንዲህ አሉ "ውሃው ንፁህም አፅጂም ነው። በርሱም ዉዱእ ማድረግ፣ ገላ መታጠብ ይፈቀዳል። ከርሱ የሚወጡን አሳዎችንና ሌሎች የባህር እንስሳዎችንም ሙተው ሳይታደኑ ከላይ ተንጣለው ቢገኙ ራሱ መብላት ይፈቀዳል።"