ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንስሳዎችና አውሬዎች ለመጠጣትና ለመሳሰሉት ስለሚመላለሱበት ውሃ ንፁህነት ብይን ተጠየቁ። ነቢዩም (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ውሃ መጠኑ ሁለት ትላልቅ እንስራዎችን የደረሰ ጊዜ ‐ 210 ሊትር የሚሆን ብዛት ማለት ነው። ‐ ብዙ ውሃ ስለሆነ ከሶስቱ ባህሪያቶቹ አንዱ በነጃሳ እስካልተለወጠ ድረስ እነርሱም ቀለሙ ወይም ጣዕሙ ወይም ሽታው እስካልተለወጠ ድረስ አይነጀስም አሉ።