ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል፦ "አንዳችሁ ከኢማም በፊት ጭንቅላቱን ቀና ያደረገ ጊዜ አላህ ጭንቅላቱን የአህያ ጭንቅላት እንዳያደርገው ወይም አላህ የሰውነት ቅርፁን የአህያ የሰውነት ቅርፅ እንዳያደርግበት አይፈራምን?!" ሶሒሕ ነው። - ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።