የአማኞች መሪ ዐሊይ ቢን አቢ ጧሊብ ረዺየሏሁ ዐንሁ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንዲህ ብሎ ተናገረ: "ከነቢዩ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- አንድን ንግግር ስናገር ከሰማችሁኝ እኔ አላሸሙርም በግልፅ ቋንቋ ነው የምነግራችሁ። በአላህ መልክተኛ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- ላይ ውሸትን ከማወራ ከሰማይ ወድቄ ብፈጠፈጥ ይሻለኛል። በኔና በሰዎች መካከል ስላለ ጉዳይ ካወራሁ ፍልሚያ ሽወዳ ነውና አሸሙሬ ላወራ እችላለሁ። ነቢዩ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- እንዲህ ሲሉ ሰምቻለሁ: "በመጨረሻው ዘመን እድሜያቸው ለጋ የሆኑ ወጣቶች፣ አስተሳሰባቸው ደካማ የሆኑ ሰዎች ይመጣሉ። ከቁርአንም ይዘው ያወራሉ አብዝተውም ቁርአንን ያነባሉ። ቀስት ኢላማውን በስቶ እንደሚወጣው እነርሱም ከእስልምና ይወጣሉ። ድንበሩንም ይጥሳሉ። ኢማናቸው ከጉሮሯቸው አያልፍም። ባገኛችኋቸው ቦታም ግደሏቸው። እነርሱን መግደል ለገደላቸው ሰው የትንሳኤ ቀን ምንዳ ያሰጠዋል።"