ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: "የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል፦ "ዘመኑ እስኪጣበብ ድረስ ሰአቲቱ አትቆምም። አመቱ እንደ ወር ይሆናል፤ ወሩ እንደ ሳምንት ይሆናል፤ ሳምንቱም እንደ ቀን ይሆናል፤ ቀኑም እንደ ሰአት ይሆናል፣ ሰአቱም የተምር ዛፍ (ዘንባባ) ቅጠል እንደሚቃጠልበት ጊዜ (ያጠረ) ይሆናል።" ሶሒሕ ነው። - አሕመድ ዘግበውታል።