ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: "የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል: ‹አላህ ይቀናል። አማኝ የሆነ ሰውም ይቀናል። የአላህ መቅናት ሰውዬው አላህ በሱ ላይ ክልክል ያደረገበትን ሲዳፈር ነው።›" ሶሒሕ ነው። - ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
explain-icon

ትንታኔ

ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) አንድ አማኝ እንደሚቀናውና እንደሚጠላው ሁሉ አላህም እንደሚቀናና እንደሚጠላ ተናገሩ። የአላህ ቅናት ምክንያትም አንድ አማኝ እንደዝሙት፣ ሰዶማዊነት፣ ስርቆት፣ አስካሪ መጠጥ መጠጣትና ሌሎችንም አላህ በርሱ ላይ ክልክል የተደረጉ ፀያፍ ተግባራትን ሲዳፈር ነው።

explain-icon

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  • የአላህ ክልከላ የተደፈረ ጊዜ ቁጣውና ቅጣቱን መፍራት እንደሚገባ እንረዳለን።