ነቢዩ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- በሐዲሠል ቁድስ አላህ እንዲህ እንዳለ ተናገሩ: ከወዳጆቼ መካከል አንድንም የኔን ወዳጅ ያወከና ያስቆጣ ከኔ ጋር ጠላት እንደሆነ አውጄያለሁም አሳውቄዋለሁም። ወሊይ ማለት: አላህን ፈሪ አማኝ ነው። አንድ ባሪያ ባለው ኢማንና ፈሪሃ አላህነት ልክ የአላህ ወሊይነት ይኖረዋል። አንድ ሙስሊም አላህ ግዴታ ያደረገበትን ትእዛዛትን መፈፀምና ክልክሎችን መተውን ያህል ወደ አላህ የሚያቃርበው ጌታው ዘንድ ተወዳጅ የሆነ ምንም ነገር የለም። አንድ ሙስሊም ወደ ጌታው ከግዴታዎች በተጓዳኝ በትርፍ ስራዎች ከመቃረብ አይወገድም የአላህን ውዴታ የሚያገኝ ቢሆን እንጂ፤ አላህ የወደደው ጊዜም አላህ እነዚህን አራት አካላቶቹን ያቀናለታል: በመስሚያው ያግዘዋል። አላህን ከሚያስደስት ነገር ውጪ ሌላ ምንም አይሰማም። በመመልከቻው ያግዘዋል። አሏህ እንዲታይ የሚወደውንና የሚያስደስተውን ነገር እንጂ ሌላ አይመለከትም። እጁንም ያግዘዋል። በእጁ አላህን ከሚያስደስት ነገር በቀር አይሰራም። አላህን ወደሚያስደስት ነገር ካልሆነ በቀር እንዳይራመድ በማድረግም እግሩንም ያግዘዋል። መልካም ነገር ወዳለበት ካልሆነ በቀርም አይንቀሳቀስም። ከዚህም ጋር አላህን አንዳች ነገር ከጠየቀው አላህ የጠየቀውን ይሰጠዋል፤ ተማፅኖውንም የሚሰማው ይሆናል። የአላህ ጥበቃ ካስፈለገውና የአሏህን ከለላ ፈልጎ ከተጠጋ ጥራት የተገባው አላህም ከሚፈራው ነገር ይጠብቀዋል።