ነቢዩ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- ቁርአንን የተማረ፣ በማንበብም ይሁን በቃል ሽምደዳ ማንበቡን ያዘወተረን ሰው ግመሉን ጉልበቷ ላይ በገመድ እንዳሰረ የግመል ባለቤት መሰሉት። ግመሏን በአግባቡ ከተቆጣጠረ እንደያዛት ይቀጥላል። ገመዱን ከፈታው ግን ግመሏ ትሄዳለችም ታመልጣለችም። የቁርአን ባለቤትም ካነበበው ያስታውሰዋል። ቁርአንን በአግባቡ ካልጠበቀ ግን ይረሳዋል። በአግባቡ ቁርአንን እስከተጠባበቀ ድረስም ሒፍዙም ከመኖር አይወገድም።