ከአማኞች እናት ዓኢሻ (ረዲየሏሁ ዐንሃ) - አላህ መልካም ሥራዋን ይውደድላትና - እንደተላለፈው እንዲህ አለች: "የነቢዩን (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንጥላቸውን እስክመለከት ድረስ በጭራሽ ሙሉ አፋቸውን ከፍተው ሲስቁ ተመልክቻቸው አላውቅም። ሲስቁ ፈገግ ብቻ ነበር የሚሉት" ሶሒሕ ነው። - ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።