ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ሁሉም ቀን በሁሉም ለአቅመ አዳም በደረሰ ሙስሊም ላይ ሁሉ በመገጣጠሚያ አጥንቶቹ ቁጥር ያህል አላህ ለሰጠው ጤንነት ለማመስገንና አጥንቶቹን መጨበጥና መዘርጋት በሚችል መልኩ ስለገጣጠመው ለአላህ ብሎ መመፅወት እንደሚገባው ገለፁ። ይህቺም ምፅዋት በመልካም ተግባራት ባጠቃላይ እንደሚፈፀምና ገንዘብ በመስጠት ላይ ብቻ እንዳልታጠረ ገለፁ። ከነርሱም መካከል: በተጣሉ ሁለት ሰዎች መካከል ማስታረቅና መፍረድ ምፅዋት ነው። መጓጓዣው ላይ ለመውጣት ለተሳነው ሰውዬ በማሰቀልህ ወይም እቃውን በመጫን ማገዝህ ምፅዋት ነው። ዚክር፣ ዱዓ ማድረግ፣ ሰላምታ ማቅረብና ሌሎችም መልካም ንግግሮች ምፅዋት ናቸው። ወደ ሶላት የምትራመዳት ሁሉም እርምጃ ምፅዋት ናት። መንገድ ላይ የሚያውክን ነገር ማስወገድም ምፅዋት ነው።