ነቢዩ - የአላህ ሶላትና ሰላም በርሳቸው ላይ ይስፈንና - ባልደረቦቻቸውን እንዲህ በማለት ጠየቁ: አንዳችሁ በየቀኑ አንድ ሺህ ምንዳ ማግኘት አይችልምን? እዛው ከተቀመጡት መካከል አንዱ "አንድ ሰው በቀላሉ በየቀኑ አንድ ሺህ ምንዳ እንዴት ሊያገኝ ይችላል?" በማለት ጠየቀ። እርሳቸውም "መቶ ጊዜ ሱብሓነላህ ይበል። በዚህም አንድ ሺህ ምንዳ ይፃፍለታል።" አሉ። አንድ መልካም ስራ በአስር ትባዛለችና። ወይም አንድ ሺህ ወንጀሉ ይራገፍለታል።