አንዳንድ ሶሐባዎች - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - ከነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ጋር ሰሑር በሉ። ከዚያም ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ለፈጅር ሶላት ቆሙ። አነስም ለዘይድ ቢን ሣቢት - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - "በአዛንና ሰሑር ተመግባቹ ባጠናቀቃችሁበት ወቅት መካከል ምን ያህል ጊዜ ነበር?" ብሎ ጠየቀው። ዘይድም - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - "ረጅምም አጭርም፣ በፍጥነት አነባበብም ዝግ ያለ አነባበብም ሳይሆን በመካከለኛ አቀራር ሀምሳ አንቀጾችን የሚያስቀራ ያህል ጊዜ ነበር።" ብሎ መለሰ።