ነቢዩ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- ከጀነት በሮች መካከል "የረያን በር" ተብሎ የሚጠራ በር እንዳለና የትንሳኤ ቀን በርሱ በኩል ጾመኞች እንደሚገቡበት ተናገሩ። ከነርሱ ውጪም በርሱ በኩል አንድም ሰው እንደማይገባበት፤ "ጾመኞች የት አሉ?" ተብሎም እንደሚለፈፍ፤ ጾመኞችም ተነስተው እንደሚገቡ፤ በርሱ በኩል ከነርሱ ውጪ ማንም እንደማይገባበት፤ የመጨረሻቸው ሰው ከገባ በኃላ እንደሚዘጋና ከዛ በኋላም በርሱ በኩል ማንም እንደማይገባበት ተናገሩ።