ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) የረመዷን ወር የገባ ጊዜ ሶስት ነገሮች እንደሚከሰቱ ተናገሩ:- አንደኛ: የጀነት በሮች ይከፈታሉ። ከጀነት በሮችም አንድም በር አይዘጋም። ሁለተኛ: የእሳት በሮች ይዘጋሉ። አንድም የእሳት በር አይከፈትም። ሶስተኛ: ሰይጣኖችና አመፀኛ ጋኔኖች በሰንሰለት ይጠፈነጋሉ። ከረመዷን ውጪ ይደርሱበት ወደነበረው አይደርሱም። ይህ ሁሉ ለዚህ ወር ልቅና፣ ከሶላት፣ ከሶደቃ፣ ከዚክር፣ ቁርአን ከመቅራትና ከዛም ውጪ ያሉ አምልኮዎች በማብዛት ላይና ከወንጀሎችና ከሀጢአቶች በመራቅ ላይ ሰሪዎችን ለማነሳሳት ነው።