ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና የአላህ ንግግር የበላይ እንድትሆን በተቻለ መጠን በሁሉም መንገድ ከሃዲያንን ለመታገልና እነርሱን ለመጋፈጥ በአቅም ልክ መታገልን አዘዙ። ከነዚህም መታገያዎች መካከል: የመጀመሪያው: እነርሱን በመታገል ገንዘብ ማውጣት ነው። ይህም መሳሪያ በመግዛት፣ ለሙጃሂዶች ወጪ በማድረግና በመሳሰሉት ነው። ሁለተኛው: ከሃዲያንን ለመፋለምና ለመከላከል በአካልና በነፍስ መውጣት ነው። ሶስተኛው: ወደዚህ ሃይማኖት በምላስ በመጥራት፣ በነርሱ ላይ ማስረጃ በማቆም፣ ከነርሱ በማስጠንቀቅና በነርሱ ላይ በመመለስ ነው።