ዐሊይ ቢን አቢ ጧሊብ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - በቀረድ ታሽቶ በተሰራ ከረጢት ከአፈሩ ያልፀዳ የወርቅ ቁርጥራጮችን ከየመን ወደ አላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ላከ። ነቢዩም (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ለአራት ሰዎች አከፋፈሉት። እነርሱም: ዑየይና ቢን በድር አልፈዛሪይ፣ አቅረዕ ቢን ሓቢስ አልሐንዞሊይ፣ ዘይድ አልኸይሊ አንነብሃሊይ፣ ዐልቀማ ቢን ዐላሠህ አልዓሚሪይ ናቸው። ከርሳቸው ባልደረባ የሆነ አንድ ሰውዬም እንዲህ አለ: "በዚህ ስጦታ ከነዚህ በበለጠ እኛ የተገባን ነን።" ይህም ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ዘንድ ደረሰና እንዲህ አሉ: "እኔ በሰማይ ላለው (አላህ) ታማኝ ሆኜ የሰማይ ወሬ ጠዋትና ማታ እየመጣልኝ አታምኑኝምን?!" አይኖቹ ገባ ገባ ያሉ፤ የጉንጩ የላይኛው አጥንት ወጣ ያሉ፤ ግንባሩም ወጣ ያለ፤ ፂሙ ሳይረዝም የበዛ የሆነ፤ ጭንቅላቱን የተላጨ፤ የታችኛውን የሰውነት አካሉን የሚሸፍነው ሽርጡ ከፍ ያለ አንድ ሰውዬ ቆመና: "የአላህ መልክተኛ ሆይ! አላህን ይፍሩ!" አላቸው። እርሳቸውም (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) "ወዮልህ! ከምድር ነዋሪዎች ባጠቃላይ አላህን ለመፍራት የተገባሁ እኔ አይደለሁምን?" አሉት። ከዚያም ሰውዬው ዞሮ ሄደ። ኻሊድ ቢን ወሊድም: "የአላህ መልክተኛ ሆይ! አንገቱን አልቅላውምን?" አላቸው። እርሳቸውም "በፍፁም! ምናልባት የሚሰግድ ሊሆን ይችላል።" አሉት። ኻሊድም: "በቀልቡ የሌለውን በአፉ የሚናገር ስንት ሰጋጅ አለ?" አለ። እርሳቸውም (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን): "እኔ የሰዎችን ቀልብ እንድሰነጥቅም ሆነ ሆዳቸውን ቀድጄ እንድመለከት አልታዘዝኩም። እኔ የታዘዝኩት ሰዎችን በውጫዊ ማንነታቸው እንድይዛቸው ነው።" አሉ። ከዚያም ሰውዬው ጀርባውን ሰጥቶ መሄዱን ሳለ እየተመለከቱት እንዲህ አሉ: "ከዚህ ሰውዬ ዘር፣ ከባልደረቦቹ ወይም ከጎሳዎቹ መካከል የአላህን መጽሐፍ በጥሩ ድምፅ አሳምረው በመቅራት ምርጥ ችሎታው ያላቸው፤ አብዝተው ከመቅራታቸውም ምላሳቸው ርጥብ የሆኑ፤ ንባባቸው ግን ከጉሮሮዋቸው የማታልፍ። ከጉሮሮ አልፋ ቀልባቸው ጋር ደርሳ የምታስተካክላቸው ያልሆነች፤ ንባባቸውን አላህ ከፍ የማያደርጋትም የማይቀበላትም፤ ቀስት ከኢላማው በላይ ፈጥኖና በቀላሉ እንደሚወጣው ከእስልምና የሚወጡ ህዝቦች ይመጣሉ።" እንዲህም ብለዋል ይመስለኛል: "በሰይፋቸው በሙስሊሞች ላይ መውጣታቸውን ብደርስበት ኖሮ እንደ ሠሙድ ህዝቦች አገዳደል ከባድ አገዳደልን እገድላቸው ነበር።"