ከአቡ ሰዒድ አልኹድሪይ ረዲየሏሁ ዐንሁ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው ነቢዩ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - እንዲህ ብለዋል፦ "ከናንተ መካከል እውነታን ተመልክቶ ወይም አውቆ ከመናገር ማናችሁንም ቢሆን ለሰዎች ያለው ፍራቻ እንዳይከለክለው።" ሶሒሕ ነው። - ቲርሚዚ፣ ኢብኑ ማጀህና አሕመድ ዘግበውታል።