ነቢዩ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - ለአማኞች እናት ለሆነችው ለዓኢሻ -አላህ መልካም ስራዋን ይውደድላትና- በእዝነት ላይ አነሳሷት። አላህ ለባሮቹ ርህሩህና ለስላሳ ነው። ለነርሱ ገርን ይፈልግላቸዋል። ለነርሱ ችግርን አይፈልግም። ከአቅማቸው በላይም አያስገድዳቸውም። የአላህ ባሪያ የሆነም ሰው ገራገር ማንነትን መላበሱንና ገርን መውሰዱን አላህ ይወድለታል። ልበ ደረቅና ስነምግባረ ብልሹ መሆንም የለበትም። አላህ በዱንያ ውስጥ እዝነትና ገራገርነትን ለተላበሰ ሰው ባማረ ሙገሳ ያወሳዋል፣ ፍላጎቱን ያሟላለታል፣ ግቡንም ያሳካለታል። በመጪው ዓለም ደግሞ ትልቅ ምንዳን ይሰጠዋል። ይህም ግትርነት፣ ድርቅናና ሀይለኝነትን ለተላበሰ ሰው ከሚሰጠው የበዛ ምንዳ ነው። ለስላሳነትን መላበስ ሌሎች ባህሪያትን መላበስ የማያመጡትን ጥቅም ይዞ ይመጣል።