ከኢብኑ ዑመር (ረዲየሏሁ ዐንሁማ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እንዲህ አሉ: «"ከአዳኝ ወይም ከከብት ጠባቂ ውሻ ውጪ የሆነ ውሻን ያሳደገ ሰው በየቀኑ ከስራው ሁለት ቂራጦች ይቀነሱበታል።" ሳሊም እንዲህ አለ: አቡ ሁረይራም የእርሻ ባለቤት ነበርና "ወይም የእርሻ ጠባቂ ውሻ ካልሆነ" ይል ነበር።» ሶሒሕ ነው። - ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።