ከአቡ ቡርዳህ አልአንሷሪይ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: እርሱ የአላህን መልዕክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እንዲህ ሲሉ ሰማ፦ "(አላህን በማመፁ ምክንያት) አላህ ያስቀመጠው የቅጣት ወሰን ካልሆነ በቀር (ስርአት ለማስያዝ) ተብሎ አንድም ሰው ከአስር አለንጋ በላይ እንዳይገረፍ።" ሶሒሕ ነው። - ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።