ከአማኞች እናት ዓኢሻ - አላህ መልካም ሥራዋን ይውደድላትና - እንደተላለፈው እንዲህ አለች: "ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) የፈጅር ሁለቱ ረከዓን (ቀብሊያ) ለመስገድ የሚያደርጉትን አይነት መጠባበቅ ለሌላ ሱና ሶላት አድርገው አይጠባበቁም ነበር።" ሶሒሕ ነው። - ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
explain-icon

ትንታኔ

የአማኞች እናት ዓኢሻ - አላህ መልካም ሥራዋን ይውደድላትና - እንዲህ ብላ ተናገረች: ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) የፈጅር ሁለቱ ረከዓን (ቀብሊያ) እጅግ ተጠባብቀውና ዘውትረው እንደሚሰግዱት ያህል ምንም ሱና ሶላት ተጠባብቀውና ዘውትረው አይሰግዱም ነበር።

explain-icon

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  • ነዋፊል (ተጨማሪ) ሶላቶች የሚባሉት: ከግዴታ ሶላቶች ውጪ ያሉ ማለት ነው። እዚህ ሐዲሥ ላይ የተፈለገውም ከግዴታ ሶላቶች በፊትና በኋላ ተከትለው የሚሰገዱ ሶላቶች ማለት ነው።
  • ሱነን አርረዋቲብ የሚባሉት: ከፈጅር በፊት ሁለት ረከዓ፣ ከዝሁር በፊት አራት ረከዓ ከዝሁር በኋላ ሁለት ረከዓ፣ ከመግሪብ በኋላ ሁለት ረከዓ፣ ከዒሻ በኋላ ሁለት ረከዓ ናቸው።
  • የፈጅር ቀብሊያ በመኖርያ ሀገር ላይም ሆነ ጉዞ ላይ ይሰገዳል። የዝሁር፣ የመግሪብና የዒሻ ቀብሊያና ባዕዲያ ሶላቶች ግን በመኖርያ ሀገር ላይ ብቻ ነው የሚሰገዱት።
  • የፈጅር ሁለቱ ረከዓ ቀብሊያ አፅንዖት የተሰጠው ተወዳጅ ሶላት ስለሆነ ችላ ሊባል አይገባውም።