ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ሶሐቦችን ከመሳደብ ከለከሉ። በተለይ የመጀመሪያ ቀዳሚ የሆኑትን ሙሃጂሮችና አንሷሮችን መሳደብን ከለከሉ። ከሰዎች መካከል አንዱ የኡሑድን ተራራ የሚያህል ወርቅ ቢመፀውት የሚያገኘው ምንዳ አንድ ሶሐባ አንድ እፍኝ እህል ‐እፍኝ የተባለው መካከለኛ ሰው በሁለት እጆቹ የሚዘግነው መጠን ነው።‐ ወይም የእፍኙን ግማሽ እህል ቢመፀውት የሚያገኘው ምንዳ ጋር እኩል እንደማይሆን ተናገሩ። ይህም ከፍተኛ ኢኽላስ ስላላቸው፣ መካ ከመከፈቱ በፊት መመፅወት እጅግ አስፈላጊ በሆነበት በዛ ወቅት በመመፅወታቸውና በመዋጋታቸው ስለቀደሙ ነው።