ከኑዕማን ቢን በሺር (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: "የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል፦ "የአማኞች እርስ በርስ የመዋደዳቸው፣ የመተዛዘናቸውና የመራራታቸው ምሳሌ እንደ አንድ የሰውነት ክፍል ነው። ከርሱ አንድ አካል የታመመ ጊዜ የተቀረው ሰውነት በእንቅልፍ እጦትና ትኩሳት ይሰቃያል።" ሶሒሕ ነው። - ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።