ከአቡ በክር አስሲዲቅ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «እኛ ዋሻ ውስጥ ሆነን ሳለን የአጋርያን እግር ከጭንቅላታችን በላይ ሆኖ ተመለከትኩት። እኔም "የአላህ መልክተኛ ሆይ: ከአጋርያኖች መካከል አንዱ ወደ እግሮቹ ቢመለከት'ኮ ከእግሮቹ ስር ይመለከተን ነበር።" አልኳቸው። እርሳቸውም: "አቡ በክር ሆይ! አላህ ሶስተኛቸው በሆኑ ሁለት ሰዎች ጉዳይ ምንድን ነው የምታስበው?" አሉ።» ሶሒሕ ነው። - ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
explain-icon

ትንታኔ

የአማኞች መሪ አቡ በክር አስሲዲቅ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - በስደት ወቅት ስለነበረው ሁኔታ ሲተርኩ እንዲህ አሉ: እኛ የሠውር ዋሻ ውስጥ ሆነን ሳለን ከጭንቅላታችን በላይ የአጋርያን እግር ሆኖ ተመለከትኩ። እኔም "የአላህ መልክተኛ ሆይ! ከአጋርያኖች መካከል አንዱ ወደ እግሮቹ ቢመለከት'ኮ ከእግሮቹ ስር ይመከተናል።" አልኳቸው። እርሳቸውም: "አቡ በክር ሆይ! አላህ በእርዳታው፣ በእገዛውና በጥበቃው ሶስተኛቸው በሆኑ ሁለት ሰዎች ጉዳይ ምንድን ነው የምታስበው?" አሉት።

explain-icon

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  • አቡበክር አስሲዲቅ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - የአላህን መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ከመካ ወደ መዲና በሚሰደዱበት ወቅት ቤተሰብና ገንዘባቸውን ትተው መጎዳኘታቸው የነበራቸውን ማዕረግ ያሳየናል።
  • አቡ በክር አስሲዲቅ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - በወቅቱ የነበራቸውን ስጋት፣ ለአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) የነበራቸውን ጥልቅ ውዴታና ጠላቶች እርሳቸውን እንዳያጠቁ የነበራቸውን ስጋት እንመለከታለን።
  • በአላህ ላይ መተማመንና ጥንቃቄን በመያዝ ጥረት ካደረጉ በኋላ በርሱ ጥበቃና እንክብካቤ መረጋጋት ግዴታ መሆኑን እንረዳለን።
  • አላህ ለነቢያቶቹና ለወዳጆቹ ትኩረት መስጠቱንና ለነርሱም በእርዳታው እንደሚንከባከባቸው እንረዳለን። አላህ እንዲህ ብሏል: {እኛ መልክተኞቻችንን፣ እነዚያንም ያመኑትን በቅርቢቱ ህይወት ምስክሮችም በሚቆሙበት ቀን በእርግጥ እንረዳለን።}
  • ይህ ሐዲሥ በአላህ ላይ የተመካ ሰው አላህ እንደሚበቃው፣ እንደሚረዳው፣ እንደሚያግዘውና እንደሚጠብቀው ያስገነዝበናል።
  • ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) በጌታቸው ላይ ያላቸው የተሟላ መመካትን እንረዳለን። እርሳቸው በአላህ ላይ የሚመኩና ጉዳያቸውን ሁሉ ወደርሱ የሚያስጠጉ ነበሩ።
  • የነቢዩን (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ጀግንነትና ቀልብና ነፍስን ያረጋጉ እንደነበር እንረዳለን።
  • ጠላትን በመፍራት ሃያማኖትን አስጠብቆ መሸሽና ሰበብንም ማድረስ እንደሚገባ እንረዳለን።
explain-icon

ምድቦች

explain-icon

ተጨማሪ