ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ሙስሊም የሆነ ሰው በዱንያ ጉዳዮቹ፣ በማዕረግ፣ በገንዘብ፣ በክብርና በሌሎችም ነገሮች በአንፃራዊ ሁኔታው ዝቅ ወዳለ ሰው እንዲመለከትና በዱንያዊ ጉዳዮች ደሞ ከርሱ የበላዩና በዱኒያ የሚበልጠው ወደሆነ ሰው እንዳይመለከት አዘዙ። ከርሱ በታች ወደሆነ ሰው መመልከት አላህ የዋለልህን ፀጋ እንዳታሳንስና ዝቅ እንዳታደርግ የሚያግዝ ነው።