explain-icon

ትንታኔ

ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ቅርብ ዘመዶችን በመዘየር ፣ በአካላዊና ገንዘባዊ ጉዳይ በማገዝና በሌሎችም መልኩ ዝምድናን በመቀጠል ላይ አነሳሱ። በተጨማሪም ዝምድናን መቀጠል ለሲሳይ መስፋትና ለእድሜ መርዘም ምክንያት መሆኑንም ተናገሩ።

explain-icon

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  • ዝምድና በማለት የተፈለገው በአባትና በእናት በኩል ያሉ ቅርብ ሰዎች ናቸው። እጅግ ቅርብ ዘመድ በሆኑ ቁጥር በዛው ልክ መቀጠሉም የተገባ ይሆናል።
  • ምንዳ በስራው አምሳያ ነው የሚሰጠው። ዝምድናውን በበጎና መልካምነት የቀጠለ ሰውን አላህም እድሜውና ሲሳዩን ይቀጥልለታል።
  • ዝምድናን መቀጠል ለሲሳይ መስፋትና መዘርጋት እንዲሁም ለእድሜ መርዘም ምክንያት ነው። ምንም እንኳ የመሞቻ ቀኑና ሲሳዩ የተወሰነ ቢሆንም ባለው ሲሳይና እድሜ በረከት ይሰፍንበታል። የተሰጠውን እድሜ ሌላው ከሚጠቀምበት በላይ ይጠቀምበታል። በርግጥ የሲሳይና እድሜ መጨመሩ እውነተኛ መጨመር ነውም ተብሏል። አላህ እጅግ አዋቂ ነው!