ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ግዴታ ሶላት ከተጠናቀቀ በኋላ አየቱል ኩርሲይን የቀራ ሰው ከሞት በቀር ጀነት ለመግባት ምንም እንደማይከለክለው ተናገሩ። ይህቺም አንቀጽ በበቀራ ምእራፍ ውስጥ የምትገኝ ሲሆን እርሷም ይህቺ የአላህ ቃል ናት: ትርጉሟ: {አላህ ከርሱ በቀር ሌላ አምላክ የለም። ህያው ራሱን ቻይ ነው። ማንገላጀትም እንቅልፍም አትይዘውም። በሰማያት ውስጥና በምድር ውስጥ ያለው ሁሉ የርሱ ብቻ ነው። ያ እርሱ ዘንድ በፍቃዱ ቢሆን እንጂ የሚያማልደው ማነው? (ከፍጡሮች) በፊታቸው ያለውንና ከኋላቸው ያለውን ሁሉ ያውቃል። በሻውም ነገር እንጂ ከእውቀቱ በምንም ነገር አያካብቡም። (አያውቁም)። መንበሩ ሰማያትንና ምድርን ሰፋ። ጥበቃቸውም አያቅተውም። እርሱም የሁሉ በላይ ታላቅ ነው።} [አልበቀራህ: 255]