ነቢዩ -የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- ከቀኑ ክፍለ ጊዜ በሶስት ወቅቶች ላይ ሱና ሶላቶችን ከመስገድ ወይም ሟቾችን ከመቅበር ከለከሉ: የመጀመሪያው ወቅት: ፀሃይ በምትወጣ ጊዜ ነው። ይህም ገና መጀመሪያ ስትወጣ ነው። ክልከላውም የጦር ርዝመት ያህል ከፍ እስክትል ድረስ ነው። ቆይታውም እስከ ሩብ ሰአት አካባቢ ይገመታል። ሁለተኛው: ፀሐይ በሰማዩ መሃል ላይ በምትሆንበት ወቅት ነው። በዚህ ወቅትም በምስራቅም ሆነ በምዕራብ አቅጣጫ ጥላ አይኖራትም። ክልከላውም ከሰማዩ መሃል ወደ ምዕራብ ዘንበል እስክትል ድረስ ነው። በዚህም ጊዜ ጥላ ወደ ምስራቅ አቅጣጫ ዘንበል ማለት ይጀምራል። ይህም የዙህር ሶላት ወቅት የሚጀምርበት ወቅት ነው። ይህ የክልከላው ወቅትም አጭር ጊዜ ነው። አምስት ደቂቃ አካባቢ ይገመታል። ሶስተኛው: ፀሐይ ለመግባት በምትዘነበልበትና በምትጀምርበት ወቅት ነው። ክልከላውም እስክትገባ ድረስ ነው።