ከኢብኑ ዐባስ (ረዲየሏሁ ዐንሁማ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል: "ሰዎች በሙግታቸው ብቻ ቢሰጣቸው ኖሮ ሰዎች የሌሎችን ገንዘብና ደም (ለመውሰድ) ይሞግቱ ነበር። ነገር ግን ማስረጃ በከሳሽ ላይ፣ መሀላ ደግሞ ክሱን ባወገዘ ሰው ላይ ማቅረብ የሚጠበቅባቸው ተደረገ።" ሐሰን ነው። - رواه البيهقي وغيره هكذا وبعضه في الصحيحين