ከእናታችን ዓኢሻ (ረዲየሏሁ ዐንሃ) - አላህ መልካም ሥራዋን ይውደድላትና - እንደተላለፈው እንዲህ ብላለች: "የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል: ‹በዚህ በመመሪያችን ውስጥ ከርሱ (ከትእዛዛችን) የሌለን አዲስ ነገር የፈጠረ ሰው እርሱ (የፈጠረው አዲስ ነገር) ተመላሽ ነው።›" ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል። በሙስሊም ዘገባ "ትእዛዛችን የሌለበትን ስራ የሰራ ሰው እርሱ (ሥራው) ተመላሽ ነው።" ሶሒሕ ነው። - ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።